ውሳኔውን ያስተላለፉት የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ እና የአቃቂ ምድብ ችሎት ናቸው፡፡

ሲሲሲሲ በመባል የሚታወቀው የቻይና ኮሙኒኬሽን እና ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ቃሊቲ በሚገኛው የባለስልጣኑ ከባድ መስመር ላይ ጉዳት ማድረሱን የተመለከተው የልደታ ምድብ ችሎት ድርጅቱ ላደረሰው ጉዳት እና ኪሳራ አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ሁለት ሺ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ብር (1,752,247) ካሳ እንዲከፍል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ራዳር ኮንስትራክሽን የተባለ ተቋራጭ በባለስልጣኑ የውሃ መስመር ላይ ያደረሰውን ጥፋት የመረመረው የአቃቂ ምድብ ችሎት ደግሞ ሶስት መቶ አስራ ሰባት ሺ ብር (317,000) ካሳ እንዲከፈል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በመንገድ ግንባታ ምክኒያት በተደጋጋሚ የሚደርሰው ጉዳት እየተስፋፋ በመምጣቱ ተቋራጮችም ሆኑ የመንገዶች ባለስልጣን ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት ለባለስልጣኑ ማሳወቅ ብሎም ለመሰረተ ልማቱ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡