የኘሮጀክቱ ስም፡- በኮንዶሚኒየም እና ሪል ስቴት አካባቢዎች ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ግንባታ ፕሮጀክት

 አስፈጻሚው አካል በአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ  ፡- በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተመረጡ ክ/ከተሞች ( የኮንደሚንየም ቤቶች ግንባታ የሚከናወንባቸው) እንዲሁም ሪል  ስቴት አካባቢዎች

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ

 ይህ ኘሮጀክት የተቀረፀበት ምክንያት የፍሣሽ ማስተር ኘላኑ ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ለተገነቡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች እና ሪል ስቴት አካባቢዎች ፍሣሻቸውን አካባቢን ሳይበክል በዘላቂነት ማስወገድ እንዲችሉ ጥናት ማካሄድ እና የግንባታ ሥራ ለማከናወን ነው፡፡

የኘሮጀክቱ ግብ

 በአጭር ጊዜ የፍሳሽ መስመር በማይደርስባቸው የኮንዶሚኒየም እና የሪል ስቴት አካባቢዎች ዘመናዊ የፓኬጅ ማጣሪያ ግንባታ በማከናወን የፍሳሽ አገለግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

በፕሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣

  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማካሄድ
  • የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ሥራ ማከናወን

የሚጠበቅ ውጤት፣ 

በተለያዩ ክ/ከተሞች የተገነቡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች እና በተጠናው የፍሳሽ ማስተር ፕላን ውስጥ ያልተካተቱ ሪል ስቴት አካባቢዎች የፍሣሽ ማስወገጃ ችግር ያለባቸው በመሆኑ ይህን ኘሮጀክት ተግባራዊ በማድረግ መፍትሄ ያገኛሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ኘሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን በኮንዶሚኒየም ቤቶች የሚኖሩ ሰዎች እና በአካባቢው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ 

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ 

  • በ2006 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ

  • በ2008 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት ግምት

  • 700,000,000 ሚሊየን ብር ገደማ እንደሚፈጅ ይጠበቃል፡፡

መግቢያ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን እ.አ.አ በ2ዐዐ2 ዓ.ም የአዲስ አበባን ፍሣሽ ማስተር ኘላን ክለሳ ማስጠናቱ ይታወቃል፡፡ ይህ የፍሣሽ ማስተር ኘላን ሁሉንም የአዲስ አበባ አካባቢዎች በተለይም የኮንደሚኒየም እና ሪል ስቴት አካባቢዎች የማያዳርስ በመሆኑ የዚህ ፕሮጀክት አስፈላጊነት ጉልህ ሆኖ ታይቷል፡፡ ስለሆነም በዚህ ማስተር ኘላን ጥናት ውስጥ ላልተካተቱ የከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ከቤቶች ለሚለቀቁ ፍሣሾች የማስወገጃ መስመሮች እና አነስተኛ ማጣሪዎች መገንባት አስፈላጊ ሆነው ስለተገኙ በ2ዐዐ6 በጀት ዓመት የጥናትና ዲዛይን ሥራ በማከናወን ወደ ግንባታ ሥራ የሚገባ ይሆናል፡፡

የኘሮጀክቱ አስፈላጊነት

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት እያደረጋቸው ካሉ ጥረቶች ውስጥ አንዱና ዋናው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ነው፡፡

መስተዳድሩ በከተማዋ በሁሉም ክ/ከተሞች ግንባታውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በቤት ግንባታ በተሰማሩ ሪል ስቴት አልሚዎች የተለያዩ ቤቶች ግንባታ ሥራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን እነዚህ አካባቢዎች በአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣና ማስተር ኘላን ውስጥ ያልተካተቱ ስለሆነ ለነዋሪዉ የፍሣሽ ማስወገጃ መስመሮችን ለመዘርጋት በተጨማሪም ማጣሪያ ለመገንባት የዚህ ኘሮጀክት መቀረጽ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

የኘሮጀክቱ ዓላማ

በተለያዩ ክ/ከተሞች የተገነቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች እና ሪል ስቴት አልሚዎች የተገነቡ ቤቶች የፍሳሽ ማስወገጃ ችግር ያለባቸው በመሆኑ የፍሳሽ መሰብሰቢያ መስመሮችን እና የፍሳሽ ማጣሪያዎችን እንዲገነቡ በማድረግ በአካባቢና በጤና ላይ የሚከሰተውን ችግር ማስቀረት ብሎም የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ሽፋን ማሳደግ ነው፡፡

የኘሮጀክቱ ግብ

በአጭር ጊዜ የፍሳሽ መስመር በማይደርስባቸው የኮንዶሚኒየም እና የሪል ስቴት አካባቢዎች ዘመናዊ የፓኬጅ ማጣሪያ ግንባታ በማከናወን የፍሳሽ አገለግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ኘሮጀክቱን ተግባራዊ ሲሆን በኮንደሚኒየም ቤቶች እና በሪል ስቴት የተገነቡ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎችየዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ ሚሆኑ ሲሆን በዚህም፡

  • ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
  • የአካባቢው ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት 

  • የቅሊንጦ፣ የደግነት፣ መካኒሳ ቆጣሪ፣ የካራ ቆሬ፣ የቦሌ ቡልቡላ፣ ቱሊዲምቱ፣ ቦሌ አራብሳ እና ገነት መናፈሻ እና ኦሮሚያ ኮንዶሚኒየም ሳይቶች ያልተማከለ ፓኬጅ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ሥራ ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

ተቋራጭ መምረጥና ተቋራጩ ግንባታውን እንደያከናውን ማድረግ እና ሥራውን መከታተል ነው፡፡

ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

ኘሮጀክቱን የሚያጠና መሐንዲስ የሚመረጥ ሲሆን፣ በተጨማሪም በግንባታ ወቅት ሥራውን የሚከታተሉ መሃንዲሶችን ያቀርባል፡፡ በባለቤቱ በኩልም እንዲሁ ሥራውን የሚከታተሉ መሃንዲሶች  ይመደባሉ፡፡

የፕሮጀክቱ ግምገማ ሥርዓት 

  • በግንባታ ሥራ ወቅት የራስ ኃይል ቡድኑ በሚያቀርበው የሥራ ክትትል ስልት መሠረት እና የጽ/ቤቱ የሥራ ሂደት ክትትል ያደርጋል፡፡

ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች

ፕሮጀክቱ ተግባራው በማድረግ ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች እንደሚከተለው ይገለፃሉ፡፡

ሀ/ ሥጋቶች

  • የወሰን ማስከበር ችግር ናቸው፡፡

ለ/ ምቹ ሁኔታዎች

  • ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድርግ የመንግስት ቁርጠኝነት፣
  • በአካከባቢው ያለው የኢንቨስትመንትና ልማት መስፋፋት፣
  • በአካባቢው የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት፤ ዘመናዊ የፍሳሽ መሰብሰቢያ እና ማጣሪያ ኘላንት የሚፈልጉ መሆናቸው፣
  • የነዋሪው ግንዛቤ እያደገ መምጣት፣

በ2008 ከላይ ለተጠቀሱት ሥራዎች ማስፈፀሚያ የሚያስፈልገው ጠቅላላ በጀት 100,488,050 ብር ሲሆን ዝርዝሩም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
17 በኮንዶሚኒየም እና ሪል ስቴት አካባቢዎች ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ግንባታ ፕሮጀክት   100,488,050 100,488,050 0 0 0
17.1 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም በቅሊንጦ፣ በደግነት፣ በመካኒሳ ቆጣሪ፣ በካራ ቆሬ እና በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም ሳይቶች ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም ግንባታ ማጠናቀቅ 652,264,712 100,000,000 100,000,000 በአጠቃላይ በሁለት ሎቶች ከሚከናወኑት ስራዎች ውስጥ እስከ 2007 በጀት አመት መጠናቀቂያ ድረስ 70 በመቶ የሲቪል ሥራዎች የሚጠናቀቅ ሲሆን የኤሌክትሮሜካኒካል አቅርቦት ስራዎች በ2008 በጀት ዓመት እስከ ነሐሴ ወር ገብተው ያልቃሉ፡፡ በዚህ መነሻነት በጀቱ ይህን ታሳቢ በማድረግ ተይዟል፡፡
17.2 የሱፐርቪዥን ሥራ ክፍያ 2,091,400 488,050 488,050 ለቀጣዩ የበጀት አመት  የሱፐርቪዥን ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡