ገቢውም ከውሃ ፍጆታ ክፍያ እና የተለያዩ የገቢ ርእሶች የተሰበሰበ ነው፡፡ በበጀት ዓመቱ ከተያዘው ዕቅድ አኳያም 86 % ማሳካት ተችሏል፡፡
የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከአራት መቶ ሰባ ሚሊዮን ብር (470,000, 000) ብር በላይ ብልጫ አለው፡፡
ለገቢ አሰባሰብ ማደግ ዋነኛ ምክንያቶችም የክፍያ ስርዓት ተደራሽነት እና ዘመናዊነት በማሳደግ ከለሁሉ ክፍያ ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመዘዋወሩ ፣የቆጣሪ ንባብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መታገዝ እንዲሁም፤
ለበርካታ ጊዜያት ውዝፍ ያለባቸው ተቋማት እና ግለሰቦች እዳቸውን እንዲከፍሉ ከፍተኛ የዘመቻ ስራ በመሰራቱ ነው፡፡