ከመጠጥ ውሃ ስርጭት መስመር ላይ በሚባክነው ውሃ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር የአለም አቀፍ ውሃ ብክነት ቀን ዛሬ ህዳር 25 ቀን በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀን 346 ቢሊየን ሊትር ውሃ ከውሃ ማሰራጫ መስመሮች ላይ ይባክናል፡፡ ይህን ብክነት በ30% መቀነስ ቢቻል በምድራችን 800 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል በዓለም አቀፍ ውሃ ማህበር የውሃ ብክነት ቡድን መረጃ ያመለክታል፡፡
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንም ከዓለም ባንክ ባገኘው ብድር በከተማዋ የሃይድሮሊክ ሞዴል የውሃ አስተዳደር ስርዓትን በመዘርጋት ከ37 በመቶ ባላይ የሆነውን የውሃ ብክነት ለመቀነስ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በዚሁ አጋጣሚም ደንበኞቻችን በውሃ መስመር ስብራት ምክንያት የውሃ መፍሰስ እና ብክነት ሲያጋጥማቸው በባለስልጣኑ ነፃ የስልክ መስመር 906 በመደወል ጥቆማ በመስጠት እንድትተባበሩ እንጠይቃለን፡፡