የኘሮጀክቱ ሥም፡      የማዕከላዊ ስካዳ ሲስተም ጥናት እና ትግበራ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- አዲስ አበባ 

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡-     በአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ እና ማእከላዊ የሆነ የውሃ ምርት እና ስርጭት ክትትል እና ቁጥጥር ስርአት መፍጠር

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን  የገጸ ምድር እና ከርሰምድር ውሃ የምርት እና የስርጭት ሁኔታ ዘመናዊ  እና  ማዕከላዌ በሆነ የመከታተያ እና መቆጣጠሪያ  ቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ የከተማዋን አጠቃላይ የውሃ ስርጭት ስርአት እንዲሻሻል ማድረግ

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የማዕከላዊ ስካዳ ሲስተም ጥናት ማከናወን
  • የጥናቱን ውጤት መነሻ በማእከላዊ ስካዳ ሲስተም ግዥ እና ትግበራ ማከናወን

ከኘሮጀክቱ የሚጠበቅ ውጤት

  • ይህ ኘሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲሆን በከተማዋ ዘመናዊ የሆነ የውሃ ምርት እና ስርጭት ቁጥጥር ስርአት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2006 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2009 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት

  • በጥናቱ የሚወሰን ይሆናል፡፡

መግቢያ

ባለስልጣን መ/ቤቱ የከተማዋን የውሃ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ከራሱ ገቢ እና ከከተማ አስተዳደሩ በጀት በማስመደብ ዘርፈብዙ የሆነ የከርሰምድር እና የገጸ ምድር ውሃ ልማት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መነሻነትም የተለያ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ በዚህም ተጨባጭ ውቴት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

ከፍተኛ ወጭ ወጥቶበት የሚመረተው ውሃ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ ጥረት እተደረገ የሚገኝ ቢሆንም ስርጭቱን ዘመናዊ በሆነ መንገድ ለመቆጣተር የሚያስችል ሲስተም ባለመኖሩ ምክንያት የሚፈለገውን ያህል ውጤታማ መሆን አልተቻለም፡፡ በመሆኑም የከርሰምድር እና ገጸ ምድር ውሃ መገኛዎችን የምርት ሂደት በቀላሉ በመቆጣጠር እና  ምርት በማይሰጡት ወይም በቀነሰባቸው ላይ አፋጣኝ መፍትሄ በማስቀመጥ በዲዛይን የተቀመጠውን የውሃ መገኛዎች የምርት መጠን ማስጠበቅ የሚቻልበትን ስርአት ለመዘርጋት እንዲሁም የተመረተውን ውሃ የስርጭት ሁኔታ በመቆጣጠር ህብረተሰቡ ፍትሃዊ የሆነ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ እንዲያስችል ይህን ፕሮጀክት መቅረጽ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የኘሮጀክቱ ዓላማ

በአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ እና ማእከላዊ የሆነ የውሃ ምርት እና ስርጭት ክትትል እና ቁጥጥር ስርአት መፍጠር

የኘሮጀክቱ ግብ

በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን  የገጸ ምድር እና ከርሰምድር ውሃ የምርት እና የስርጭት ሁኔታ ዘመናዊ  እና  ማዕከላዌ በሆነ የመከታተያ እና መቆጣጠሪያ  ቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ የከተማዋን አጠቃላይ የውሃ ስርጭት ስርአት እንዲሻሻል ማድረግ

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ይህ ኘሮጀክት ሲጠናቀቅ ዘመናዊ የሆነ የውሃ ምርት እና ስርጭት ስርአት እንዲኖር ከማስቻሉም ባሻገር የተሻለ የውሃ ስርጭት ስርአት እንዲኖር በማስቻል ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል ይሆናል፡፡

በኘሮጀክቱ ሂደት የሚጠበቁ ውጤቶችና ተጠቃሚዎች መካከል

  • አጠቃላይ የውሃ ምርት እና ስርጭት ሁኔታ ዝርዝር ዳሰሳ ጥናት ይደረጋል፡፡
  • በተለያየ ምክንያት አገልግሎት የማይሰጡ የውሃ መገኛዎች እንዲለዩ እና የመፍትሄ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ይደረጋል
  • ተግባራዊ የሚደረገው ሲስተም ዘመናዊ እና አዲስ ቴክኖሎጂ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በስራው ላይ ለሚሳታፉ ባለሙያዎች ወሳኝ የእውቀት ሽግግር ምእራፍ ይሆናል፡፡

ከኘሮጀክቱ መጠናቀቅ በኋላ የሚገኙ ውጤቶችና ጥቅሞች

  • በአሁን ሰአት በስርጭት ስርአቱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች በዘመናዊ ስርአት ተለውጠው ማእከላዊ የሆነ የክትትል እና ቁጥጥር ስርአት ይፈጠራል
  • ማእከላዊ እና ዘመናዊ በሆነ መንገድ ሁሉንም የውሃ መገኛዎች ለመከታተል እና ለመቆጣጠር የሚያስችል ሲስተም ይዘረጋል
  • ህብረተሰቡ የተሸለ የውሃ ስርጭት እንዲኖር በማስቻል ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችላል
  • የአ/አ ከተማን አለምአቀፋዊ እሴት ይበልጥ ያስጠብቀል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • የማዕከላዊ ስካዳ ሲስተም ጥናት ሥራ ማከናወን
  • ለትግበራ ሥራው የተቋራጭ ቅጥር ሂደት ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

  • በቴክኖሎጂው በቂ ልምድ ያላቸው ኢንተርናሽል አማካሪዎችን በመጋበዝ የጥናት ስራው ሌሎች ሀገሮችን ተሞክሮ ባካተተ መልኩ እንዲከናወን ማድረግ
  • በጥናቱም ሆነ በትግበራው ሂደት የእውቀት ሽግግር እንዲፈጠር ማድረግ
  • ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፍተር ስራዎች በታለመላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ማድረግ
  • የፕሮጀክቱ ትግበራ በጠንካራ የክትትል እና ድጋፍ ስርአት እንዲደገፍ ማድረግ

ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግበአቶች

  1. ለፕሮጀክቱ ትግበራ የሚያስፈልጉ የተለያየ ሙያ ያላቸው ባለሙያዎች፣
  2. ፕሮጀክቱን ለመተግበር የሚያስፈልግ በጀት

የክትትልና ግምገማ ስርዓት

የኘሮጀክቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ የታቀደለትን ጊዜ የጠበቀና ስርዓቱን የተከተለ እንዲሆን የሪፖርት፣ የሳይት ጉብኝት እና መሰል የክትትልና የግምገማ ሥርዓት የሚዘረጋ ይሆናል፡፡

አጠቃላይ እና ዝርዝር በጀት

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
31 የማዕከላዊ ስካዳ ሲስተም ጥናት ፕሮጀክት   9,147,700 0 9,147,700 0 0
31.1 የማዕከላዊ ስካዳ ሲስተም ጥናት ሥራ ማከናወን 7,219,700 1,147,700 1,147,700 ጥናቱ የ6 ወር ሲሆን በውሉ መሰረት በ2008 በጀት ዓመት ለጥናት ሥራው የሚከፈል በጀት ነው፡፡
31.2 የማዕከላዊ ስካዳ ሲስተም ትግበራ ሥራ  ማከናወን 40,000,000 8,000,000 8,000,000 በሚገባው ውለታ መሠረት ለቅድመ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡