የኘሮጀክቱ ሥም፡    የሦስተኛው መጠጥ ውሃ ክለሳ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በማሳደግ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- ከዚህ በፊት ጥናቱ የተጠናቀቀው የሦስተኛው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተግባራዊ የሚሆንበትን አማራጭ ጥናት በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ እንዲሆን ይደረጋል

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • ወቅታዊውን የከተማዋን የውሃ አቅርቦት ሁኔታ ማጥናትና የነባር ውሃ መገኛዎችን አቅም በመፈተሸ ለወደፊቱ አቅርቦት ያላቸውን አስተማማኝነት መገምገም፣
  • ተጨማሪ ውሃ ለማምረት እየተከናወኑ ያሉ የማስፋፊያና አዳዲስ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በመገምገም በውሃ አቅርቦቱ ላይ የሚኖራቸውን ሚና መለየት፣
  • የሦስተኛው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ታሳቢ ያደረጋቸውን የዲዛይን ፓራሜትሮች መገምገምና እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያዎችን ማድረግ፣
  • አጠቃላይ የከተማውን ተጨማሪ የውሃ ፍላጎት መጠን ማስላት
  • የሚፈለገውን ተጨማሪ ውሃ ለማግኘት በሚያስችል መልኩ የሦስተኛው መጠጥ ውሃፕሮጀክት ለመተግበር የሚቻልባቸውን አማራጮች ማቅረብ፣
  • ጥናቱ አሁን ካለው የአዲስ አበባና አካባቢው ከተሞች መስፋፋት አንጻር መተግበር የሚያስችሉ ሁኔታዎች መኖራቸውን መገምገም፣

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2004 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2008 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 60,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

የከተማዋን የወደፊት የውኃ አቅርቦት ፍላጎት መሠረት ያደረገ ጥናት ከዚህ በፊት የተጠና ሲሆን በጥናቱ መሠረትም ይህ ፕሮጀክት ቢተገበር እስከ 20 ዓመታት ድረስ ያለምንም ችግር የከተማዋ የውኃ ፍላጎት መሟላት እንደሚችል ያሳያል፡፡ ሆኖም በተለያዩ ምክያቶች የተነሳ ጥናቱ እስካሁን ድረስ ሳይተገብር ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ጋር በተያያዘ ጥናቱን በመከለስ የሚተገበርበትን አማራጭ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ለዚህም ያስችል ዘንድ ይህን ፕሮጀክት ተቀርጿል፡፡

የሥራው አስፈላጊነት

ይህ ኘሮጀክት ተፈጻሚ ሲሆን የሦስተኛው መጠጥ ውኃ ተግባራዊ የሚሆንበትን አማራጭ በማስቀመጥ ከዚህ በፊት የተጠናው ጥናት ወደ ትግበራ እንዲገባበት የሚያስችል ይሆናል፡፡

የሥራው ዓላማ

የሦስተኛው መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የሚተገበርበትን አማራጭ ጥናት በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ ማድረግ ነው፡፡

የሥራው ግብ

ከዚህ በፊት ጥናቱ የተጠናቀቀው የሦስተኛው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተግባራዊ የሚሆንበትን አማራጭ ጥናት በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ እንዲሆን ይደረጋል

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

  • የሦስተኛውን መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ለመተግበር የሚያስችል ጥናት
  • የከተማዋ ሕብረተሰብ ተጨማሪ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ያገኛል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • የአማካሪ ቅጥር በመፈጸም ዝርዝር የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

  • የዝርዝር ጥናት ዲዛይን ሥራ የሚያከናውን አማካሪ መቅጠርና የጥናት ሥራውን መከታተል፤

ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

  • ዝርዝር ጥናቱን የሚያጠና አማካሪ የሚቀጠር ሲሆን አስፈላጊ ባለሙያዎችን በሙሉ አማካሪ ድርጅቱ ያቀርባል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርአት

  • የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ለመከታተል ሳምንታዊና ወርሃዊ ሪፖርቶችን መከታተል፡፡
  • የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት የዕቅዱን አፈፃፀም በየወሩ በመገምገም እቅዱን መከለስ

በጀት /ጠቅላላና ዝርዝር ወጪ/

ይህንን ሥራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የማዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
7 የሦስተኛው መጠጥ ውኃ ክለሳ ፕሮጀክት   60,000,000 10,000,000 0 0 50,000,000
7.1 ዝርዝር የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን 60,000,000 60,000,000 10,000,000 50,000,000 ጥናቱ የ9 ወር ሲሆን በውሉ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ለጥናት ሥራው የሚከፈል በጀት ነው፡፡