የተጎበኙት መሰረተ ልማቶች የመካኒሳ ቁጥር ሁለት የጋራ መኖሪያ ቤት የተገነባው ያተማከለ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ እና የቃሊቲ ማጣሪያ ጣቢያን ናቸው ፡፡

የጉብኝቱ ዋና አላማ አባላቱ በፍሳሽ ዘርፍ የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን በማየት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡
በተለይም በቀን መቶ ሺኅ ሜ.ኪዩብ የማጣራት አቅም ያለው የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ በከፍተኛ ወጪ ተገንብቶ አገልጎሎት እየሰጠ ቢሆንም እያጣራ ያለው ከግማሽ ያነሰ ነው ፡፡

ማጣሪያ ጣቢያው በሙሉ አቅሙ እንዲያገለግል ህብረተሰቡ በተዘረጉ መስመሮች የቤት ለቤት ቅጥያ ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡

ከተጠቃሚዎቹ መካከል በመካኒሳ ቅርንጫፍ ስር ያሉትን በርካታ አከባቢዎች (ወተት ቤት፣አሚጎ፣ቤተል፣ አንበሳ ገራጅ ፣ ቫቲካን፣አየርጤና፣ዩቴክ ሪልእስቴት፣ አለም ባንክ እና ሌሎችም የፍሳሽ መሰረተ ልማት ተዘርግቶ የቤት ለቤት ቅጥያ ያላሰሩ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ የፎረም አባላቱ ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ነው፡፡

በተጨማሪም በፍሳሽ መሰረተ ልማቶች ውስጥ ባእድ ነገሮችን መጣል የሚደርሰውን ጉዳት በመረዳት የጋራ ግንዛቤ ኖሯቸው ህብረተሰቡን ባገኙት መድረክ ሁሉ እንዲያሳቅውቁ ለማድረግ ነው፡፡

ጎብኚዎቹም ባዩት መሰረተ ልማት መደሰታቸውን ገልጸው ተጠቃሚነቱ እንዲስፋፋ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡