ባለስልጣኑ በ2013 በጀት ዓመት ከ781 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን በጀት በጥቃቅን እና አነስተኛ በ169 አዲስ እና ነባር ማህበራት ለተደራጁ ከ1700 በላይ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ተዘጋጅቷል፡፡
ለስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር በከተማ ደረጃ ለተያዘው የድህነት ቅነሳ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከነባር ማህበራት በተጨማሪ በተያዘው በጀት ዓመት ከ64 በላይ ለሚሆኑ አዲስ ማህበራት የስራ ትስስር ለመፍጠር የቅድመ ዝግጅት ስራ ማጠናቀቁን የሦስተኛ ወገን ስራ ዕድል ፈጠራና መረጃ ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋሲሁን ዘውዴ ገልፀዋል፡፡
የውሃ እና ፋሳሽ ማንሆል ማምረት፣ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ እና ቅጥያ፣ ያልተጠናቀቁ መፀዳጃ ቤቶች ፣ አጥር ፣ የጥበቃ ቤት፣ ግምጃ ቤት እና የጄኔሬተር ቤት ግንባታ የስራ እድል የሚፈጠርባቸው የስራ ዘርፎች ናቸው፡፡
በተጨማሪም ከ100 በላይ ለሚሆኑ አዲስ የቆጣሪ አንባቢ ማህበራት እና ከ384 በላይ ለሆኑ የቁፋሮ ማህበራት የስራ ትስረስር እንደሚፈጠር አቶ ዋሲሁን ዘውዴ ገልፀዋል፡፡
ባለስልጣኑ የስራ ዕድል ፈጠራውን እያከናወነ የሚገኘው ከከተማ አስተዳደሩ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ እና ከወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር በመቀናጀት ነው፡፡