በጉብኝታቸው ወቅትም ባለስልጣኑ እያካሄዳቸው ያሉት ተግባራት መልካም መሆናቸውን ጠቅሰው በቀጣይ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ በሂደቱም ቢሯቸው ለባለስልጣኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራስኪያጅ ኢንጅነር ዘርይሁን አባተ ባለስልጣኑ ከገጸ ምድር የሚያገኛቸውን የውሃ ሀብቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ በአከባቢ ጥበቃ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

እስካሁን በድሬ እና በለገዳዲ ግድብ ዙሪያ 15ሺኅ የሚደርሱ የተለያዩ አይነት ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 6ሺኅ የአፕል ችግኞች እና አንድ ሺኅ ልዩ የሎሚ ችግኝ ይገኙበታል ፡፡

ባለስልጣኑ ችግኞቹን ከመትከል ባለፈ ለታለመላቸው አላማ ይውሉ ዘንድ ክብካቤ እና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ዋና ስራአስኪያጁ አስረድተዋል፡፡

በአካባቢ ጥበቃ ስራው ከ50 በላይ ለሚሆኑ የአካባው ነዋሪዎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡

በተጨማሪም በግድቡ አካባቢ ነዋሪ ለሆኑ 12 ማህበራት ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በስራው ላይ እንዲሰማሩ ተደርጓል፡፡