የኘሮጀክቱ ሥም፡    የአዳዲስ ውሃ ተቋማት ግንባታ ኘሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡-በአዲስ አበባ የገጠር ከተማዎችና በአጐራባች የኦሮሚያ ገጠር ቀበሌዎች

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በማሳደግ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- የመለስተኛና ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ የመስመር ዝርጋታ ሥራ በማጠናቀቅ ወደ ሥርጭት ሲስተም በማስገባት የከተማዋ የንፁ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ ቁጥር እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የ25 መለስተኛ ጉድጓዶች ቁፋሮና ፓምፕ ቴስት ሥራ፣
  • የ19 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮና ፓምፕ ቴስት ሥራ ማከናወን፣
  • የውኃ ማስተላለፊያ መስመር ኔትወርክ፣ ማጠራቀሚያ ጋንና የግፊት መስጫ ጣቢያ እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ጥናት ማካሄድ
  • የስርጭት (Transmission Line) መስመር እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ጥናት ማካሄድ፣
  • ለተቆፈሩ ጉድጓዶች ወደ ማጠራቀሚያ ጋኖች መሰብሰቢያ (Collector pipes) የውኃ መስመር ዝርጋታ ሥራ፣
  • የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች የዕቃ ግዥና ግንባታ፣
  • የቧንቧና መገጣጠሚያ እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ውኃ ማጠራቀሚያ ጋን ግዥ
  • የማጠራቀሚያ ጋን እና ሌሎች አስፈላጊ የህንጻ ግንባታ ሥራዎች
  • የዋና መስመር ዝርጋታ ሥራ፣
  • የፓምፕና ጥበቃ ቤት ግንባታ እንዲሁም የትራንስፎርመር ተከላ ሥራ
  • ከጉድጓድ ቁፋሮና መስመር ዝርጋታ ጋር በተያያዘ የካሳ ክፍያ
  • የግንባታ ሱፐርቪዥን ሥራ

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2001 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2008 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 1,500,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

 

መግቢያ

የአዲስ አበባ ከተማን የውሃ ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት እቅድ ጐን ለጐን በአለም ባንክ በጀት የሚሰራ ተጨማሪ ሥራዎችም በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ ኘሮጀክቶቹ በአዲስ አበባ ገጠራማና በአነስተኛ መተዳደሪያ አቅም ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ያቀፈ ሲሆን በተለይ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የከተማው ነዋሪዎች በመገንባት ላይ ለሚገኘው የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም ተጠቃሚዎችም የተሻለ የውሃ አቅርቦት ማድረግን አላማ ያደረገ ኘሮጀክት ነው፡፡

ኘሮጀክቱ በ 2ዐዐዐ ዓመት በተመረጡ አካባቢዎች ካስቆፈራቸው 25 መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓዶች በተጨማሪ 19 ጥልቅ ጉድጓዶችን ለማስቆፈር የታለመ ሲሆን አጠቃላይ እንቅስቃሴው የጉድጓድ ቁፋሮና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች አቅርቦት እንዲሁም ከዚህ በፊት ለተቆፈሩ መለስተኛ ጉድጓዶች የፓምኘና መገጣጠሚያዎች እና የማጠራቀሚያ ጋን ግዥን ያቀፈ ነው፡፡

የኘሮጀክቱ አስፈላጊነት

ለብዙ ጊዜ የከተማው ሕዝብ መሠረታዊ ችግር ሆኖ የኖረውን የውሃ አቅርቦትና ስርጭት ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት በጀት በተጨማሪ የሚሰራው ይህ የአለም ባንክ ኘሮጀክት በተለይ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈ ሲሆን በከተማው ውስጥ በሁሉም የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙትን የሕብረተሰብ ፍላጐት የሚያቅፍ ኘሮጀክት መቀረጹ ለመልካም አስተዳደር ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደረውን ሕብረተሰብ በቀላሉ የንፁሕ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ስለማያደርገው ለሕብረተሰብ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

የኘሮጀክቱ ዓላማ

የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በማሳደግ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣

የኘሮጀክቱ ግብ

በቀን እስከ 60 ሺህ ሜ.ኪዮብ ውኃ ለማምረት የሚያስችሉ የ19 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮና ተያያዥ ሥራዎች ይጠናቀቃል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ኘሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን በአካባቢው በአነስተኛ ገቢ የሚኖረው የሕብረተሰብ ክፍል ቅድሚያ ተጠቃሚ ሲሆን የንፁሕ ውሃ ለማግኘት ብዙ መንገድና ብዙ ወጪ የማያወጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በቀላሉ ተጠቃሚ ይሆኛሉ፡፡ በዚህም የአካባቢው ሕብረተሰብ የኑሮ ደረጃው ይሻሻላል፣ በተበከለ ውሃና በውሃ ወለድ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎች ይቀንሣሉ፡፡ በአጠቃላይ የሕብረተሰቡ ምርታማነትና የኑሮ በማሣደግ በኩል ከፍተኛ ውጤት ይኖረዋል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • ለውኃ ሥርጭቱ ችግር የማይፈጥሩ ቀሪ ሥራዎችን ማጠናቀቅ፣

የአፈጻጸም ስልቶች

  • ከሚቆፈሩት ጉድጓዶች ውስጥ በቀላሉ ወደ ሲስተም የሚገቡ ጉድጓዶች በመለየት የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ተከላ እና ተያያዥ ሥራዎች ሥራ ማከናወን

ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግበአቶች

  • ኘሮጀክቱን የሚያጠናና በግንባታም ወቅት ሥራውን የሚከታተል አማካሪ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ በባለቤቱ በኩልም እንዲሁ ሥራውን የሚከታተሉ መሃንዲሶች ይመደባሉ፣

የአካባቢና የማህበራዊ ትንታኔ

በአማካሪ ድርጅት ከቀረበው አንዱና ዋነኛው ኘሮጀክቱ ሊያስከትል የሚችለው አካባቢያዊ ተጽዕኖ ግምገማና ኘሮጀክቱን ተከትሎ የሚመጡ የኢኮኖሚና ሶሻል በጎና አሉታዊ ተጽእኖዎች ናቸው፡፡

የተጠናውን ጥናት መሠረት በማድረግ አሉታዊ ተጽኖዎችን ለማስቀረትና በጎ ጐኖችን ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ ያሰራል፡፡

የክትትልና ግምገማ ስርዓት

የኘሮጀክቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ጥራቱን የጠበቀና ስርዓቱን የተከተለ እንዲሆን የተለያዩ የክትትልና የግምገማ ሥርዓት የተዘረጋ ሲሆን ከዚህም አንዱ ለራሱ የሆነ አማካሪ በመቅጠር የሱፐርቪዥን ሥራው በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥጥር እየተደረገበት ይገኛል፡፡

አጠቃላይ እና ዝርዝር በጀት

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
41 የአዳዲስ  ውኃ ተቋማት ግንባታ ፕሮጀክት (ፌዝ 3A)   63,937,256 63,937,256 0 0 0
41.1 የ9.4 ኪ.ሜ.የዋና መስመር እና ተያያዥ ሲቪል ሥራዎች ቀሪና የመያዥያ ክፍያ መፈጸም 110,676,751 11,332,445 11,332,445 በውሉ መሰረት በ2008 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሥራ ተቋራጮች የሚከፈል ቀሪና መያዥያ ክፍያ ነው፡፡
41.2 የ44.8 ኪ.ሜ የማሰባሰቢያ መስመር ዝርጋታ ሥራ ቀሪና የመያዥያ ክፍያ መፈጸም 156,878,360 23,531,754 23,531,754
41.3 የ30.9 ኪ.ሜ. የመዳረሻ መንገድ የመያዥያ ክፍያ መፈጸም 138,345,723 6,917,286 6,917,286
41.4 የኤሌክትሮሜካኒካል ዕቃ አቅርቦትና ተከላ ሥራ የመያዥያ ክፍያ መፈጸም 32,905,520 7,694,653 7,694,653
41.5 በጉድጓዶች አካባቢ ለተከናወነ የሲቪል ሥራ የመያዥያ ክፍያ መፈጸም 89,222,363 4,461,118 4,461,118
41.6 የሱፐርቨዥን ክፍያ ለውኃ ሥራዎች ያልተከፈለ 85,975,240 10,000,000 10,000,000 ለውኃ ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ባለስልጣን በውሉ መሠረት ከሪምበረሰብል ኮስት ጋር እና ከልወሰደው ክፍያ ጋር ተይይዞ በቀጣ ለሚከፈል ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡