የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ በአለም ባንክ ብድር ያሰራው የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ በሙሉ አቅሙ እንዲያጣራ 80 ኪሎ ሜትር መስመር ተዘርግቶ የቤት ለቤት ቅጥያ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ፡፡

በተፋሰሱ ስር የሚገኙ ነዋሪዎችን የዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘረጋ 80 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ ማሰባሰቢያ መስመር ላይ ከ550 በላይ ማንሆል ተሰርቶ የብረት ክዳን ቢበጅለትም ከቃልቲ አስከ አንፎ ባለው መስመር ብቻ 180 ማሆል ክዳን ተሰርቋል ፡፡

በሌሎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ በተሰራ ያልተማከለ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የማንሆል ክዳን ሙሉ ለሙሉ እየተሰረቀ የህዝብ ሀብት እየወደመ ነው፡፡

የማንሆል ክዳን ስርቆቱ ብቻ ሳይሆን ማንሆሉ ውስጥ ድንጋይ በመጨመር ፍሳሹ እንዳይሄድ ከማድረግም ባሻገር በፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያው የማይፈለጉ ባእድ ነገሮች እንዲገቡ እና ማጣሪያ ጣቢያው አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ ምክኒያት እየሆኑ ነው፡፡

ይህ የህዝብ ሀብት የሆነውን መሰረተ ልማት የመጠበቅ ሀላፊነት የሁሉም ዜጋ መሆኑን በመረዳት በዚህ ህወጥ ተግባር ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን በማጋለጥ እና ሀብቱን በመጠበቅ ከባለስልጣኑ ጎን እንድትቆሙ ጥሪውን ያስተላፋል፡፡