የኘሮጀክቱ ሥም፡    የፕሮጀክት ጽ/ቤት ግንባታ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ክ/ከተማ

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የፕሮጀክት ጽ/ቤት ግንባታ በማከናወን ምቹና  የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት፣

ግብ ፡- የፕሮጀክት ጽ/ቤት ግንባታ በማከናወን የመ/ቤቱን ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን፣
  • የፕሮጀክት ጽ/ቤት ግንባታ

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2007 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2009 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 50,000,00 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

 

መግቢያ

 

ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጥሩ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት የሚያደርግ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በአገልግሎት ቦታ ችግር ምክንያት የታሰበውን ውጤት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ በመሆኑም የተለያዩ የአገልግሎት መስጫዎችን በመገንባት ችግሩን ለመፍታት ታቅዷል፡፡ የፕሮጀክቱ መተግበር የአገልግሎት ተጠቃሚው ህብረተሰብ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኝ ብሎም የጽ/ቤቱ የማሰፈፀም አቅምን ከፍ እንዲል ያደርገዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

ይህ ፕሮጀክት የጽ/ቤቱን አገልግሎትን በማቀላጠፍ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት በኩል በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

  • የ1 ፕሮጀክት ጽ/ቤት በመገንባት ጥራቱን የጠበቀ እና ለሠራተኞች ምቹ የሆነ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ፣

የፕሮጀክቱ ግብ

  • የፕሮጀክት ጽ/ቤት ግንባታ በማከናወን የመ/ቤቱን ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

የሚጠበቁ ውጤትና ተጠቃሚዎች

  • የአካባቢው ሕብረተሰብ በቅርበት የተሟላ አገልግሎት ያገኛል፣
  • የባለሥልጣን መ/ቤቱ የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት የማስፈፀም አቅሙን ይበልጥ ያሳድጋል፣
  • በየጊዜው ለቢሮ ኪራይ የሚወጣውን ገንዘብ በማስቀረት የመንግሥትን በጀት በአግባቡ ለመጠቀም ያስችለዋል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • ለፕ/ጽ/ቤት የግንባታ ቦታ ማግኘት ሥራ በ3 ወር ውስጥ እስከ ሐምሌ 30 ድረስ ማግኘት፣
  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን፣
  • ለግንባታ ሥራው የግንባታ ፍቃድ ማግኘት ሥራ፣
  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም 5 በመቶ የፕ/ጽ/ቤት ግንባታ ሥራ ማከናወን፣

የአፈፃፀም ስልቶች

  • ቀጥተኛ የፕሮጀክት ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ሥራዎች የዕለት ተዕለት ቁጥጥር ማካሄድ፣

ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብአቶች

  • ተቆጣጣሪ መሐንዲስ
  • ሲሚንቶና የሲሚንቶ ውጤቶች፣ የግንባታ ብረቶች፣ ማናቸውም ተጓዳኝ የግንባታ ግብአቶች፣
  • የስለጠነ ባለሙያ፣

የአካባቢና ማህበራዊ ትንታኔ

የግንባታ ሥራዎች በሚገኙበት አካባቢ ለሚኖሩ አነስተኛና ጥቃቅን ድርጅቶች ለቀን ባለሙያዎችና ለአገር ውስጥ ከፍተኛና መለስተኛ ተቋራጮች ጥሩ የሥራ ዕድል ስለሚከፍት ጥሩ የማህበራዊ እሴት ይኖራቸዋል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርዓት

  • የፕሮጀክቶችን እንቅስቃስ ለመከታተል ሳምንታዊና ወራዊ የሳይት ሪፖርቶችን መከታተል፣
  • ወርሃዋ የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት ዕቅዱንና አፈፃፀሙን በየወሩ በመገምገም፣
  • የፕሮጀክቶዡን እንቅስቃሴ ዕቅድንና አፈፃፀሙን በማቀናጀት ለሚመለከተው አካል መላክ፣
  • የፕሮጀክቶች ዕቅድ ከፊዚካል አፈፃም ጋር አለመጣጣም ሲገኝ እቅዱን መከለስ፡፡

ሥጋትና ምቹ ሁኔታዎች

የፕሮጀክት ጽ/ቤት ግንባታ በታሰበላቸው ግብ ለመሰራት የሚያጋጥሙ ዋና

ሥጋቶች

  • የግንባታ ግብአቶች በበቂ ሁኔታና በታሰበ ጊዜ አለመገኘት፣
  • የግንባታ ግብአቶች ዋጋ መጨመር፣
  • በቂ የሰለጠነ ባለሙያ አለማግኘት፣
  • የግንባታ ቦታ በወቅቱ አለማግኘት

  ምቹ ሁኔታ

  • መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት
  • ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በባለሙያዎች ለፕሮጀክቶቹ ተግባራዊነት በሙሉ አቅማቸው መትጋት፣

የ2008 በጀት ዓመት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ በጀት 14,598,060 ሲሆን ይህ በጀት ከዚህ በፊት ባለሥልጣን መ/ቤቱ ያሰራቸውን ቅ/ጽ/ቤቶች መነሻ ዋጋ እና አሁን ያለውን ወቅታዊ ዋጋ መነሻ በማድረግ የተያዘ ነው፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
28 የፕሮጀክት ጽ/ቤት ጥናት እና ግንባታ ፕሮጀክት   14,598,060 14,598,060 0 0 0
28.1 የዲዛይን ጥናት ማከናወን 22,000 22,000 22,000 በ2007 በጀት አመት ለሚከናወን የጥናትና ዲዛይን ሥራ በውል ስምምነቱ መሠረት ለመክፍል የተያዘ በጀት ነው፡፡
28.2 የተቋራጭ ቅጥር በመፈፀም የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት  ግንባታ ማከናወን 48,000,000 14,400,000 14,400,000 በበጀት ዓመቱ በሚገባው ውለታ መሠረት የቅድመ ክፍያ 20 በመቶ ለሚከፈል ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ ( ስራው ለ18 ወራት እንደሚከናወን ታሳቢ ተደርጓል፡፡)
28.3 የሱፐርቪዥን ሥራ ክፍያ 459,540 51,060 51,060 በውል ስምምነቱ መሠረት በየወሩ ለሚያካሄደው የሱፐርቪዥን ሥራ በየወሩ የሚከፍል ሲሆን በዚህ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ለ2 ወር ለሚከፍል ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፤
28.4 የካሳ ክፍያ 125,000 125,000 125,000 ከፕሮጀክት ትግበራው ጋር በተያያዘ ለሚከፈል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡