የፕሮጀክቱ ሥም፡የBio-gas የህዝብ መጸዳጃ ቤት ጥናትና ግንባታ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል ፡ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፕሮጀክት ጽ/ቤት

ፕሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ ፡ በተለያዩ በተመረጡ የከተማዋ አካባቢዎች

የስራው ጠቅላላ አላማ ፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ነዋሪዎች የመፀዳጃ እና የሻወር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣

የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ግብ ፡ በከተማዋ የሚታየውን የመፀዳጃ እና የሻወር ቤት ችግር ለመቅረፍ የህዝብ መፀዳጃ ቤት እና የሻወር ቤት ገንብተን የትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡና አገልግሎቱን ለሚጠቀሙ የህብረተሰብ አካላት እንዲሁም የትናንሽ ሸቀጥ እና የሊስትሮ አገልግሎት ለሚሰጡ ሰዎች ንፅህናው የተጠበቀ የመፀዳጃ እና የሻወር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡

የሚከናወኑ ተግባራት፡

  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ
  • የመፀዳጃ ቤት ግንባታ
  • የሻወር ቤት ግንባታ

ፕሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡ 2005 ዓ.ም

ፕሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡ 2007 ዓ.ም

የፕሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት ግምት፡ 35,500,000.00 ብር

መግቢያ

የአንድ ከተማን የንፅህና ጉድለት ከሚያስከትሉ ነገሮች አንዱ በቂና ንፅህናቸው የተጠበቁ ዘመናዊ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች በተለያዩ ቦታዎች ባለመኖራቸው ነው፡፡ ይህ ችግር በከተማችን በሰፊው ጎልቶ ይታያል፡፡ ከተማዋ የአፍሪካ እና የኢትዮጵያ መዲና ከመሆኗ የተነሳ የሚጠበቅባትን የንፅህና ደረጃ ላይ አትገኝም፡፡ በተለይ በብዛት የህዝብ እንቅስቃሴ የሚታይባቸው አካባቢዎች የህዝብ መፀዳጃ ቤትና የሻወር ቤት አገልግሎት የሚሰጡ ቤቶች ባለመገንባታቸው ህብረተሰቡ ባገኘው ስርቻ እየተፀዳዳ አካባቢውን ፅዱ፣ማራኪና ለስራ ምቹ የማይሆኑባቸው ምክንያቶች ብዙ ናቸው፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የፕሮጀክቱ መተግበር ለነዋሪው ህብረተሰብ ብሎም በአካባቢው የሚገኙ አገልግሎት ሰጪዎችና ተጠቃሚዎች እንዲሁም መፀዳጃ ቤቱን ለሚያስተዳድሩ አካላት ሰፊ ጠቀሜታ የሚሰጥ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

ሥራው፡-

  • በየአካባቢው አገልግሎት የሚሰጡ እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እፎይታን ይፈጥራል፤
  • አካባቢውን ፅዱ፣ማራኪና ለስራ ምቹ እንዲሆን በማድረግ የአካባቢ ብክለትን ይቀንሳል፤
  • መፀዳጃ ቤቱን ለሚያስተዳድሩ አካላት የስራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን የማስተዳደር አቅም ይፈጥርላቸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አላማ

  • የህዝብ እንቅስቃሴ የሚበዛባቸው አካባቢዎችን የመፀዳጃ ቤትና የሻወር ቤት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፤

የፕሮጀክቱ ግብ

  • በተመረጡ ቦታዎች ላይ ለስራው የሚያስፈልጉ ማናቸውም ግብዓቶችን በመጠቀም ለአካባቢው ተጠቃሚ ህብረተሰብ ንፅህናቸው የተጠበቁ ዘመናዊ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችና እና ሻወር ቤቶችን ገንብቶ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

  • በአካባቢው አገልግሎት የሚሰጡ እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እፎይታን ይፈጥራል
  • አካባቢውን ፅዱ፣ማራኪና ለስራ ምቹ እንዲሆን በማድረግ የአካባቢ ብክለትን ይቀንሳል፤
  • መፀዳጃ ቤቱን ለሚያስተዳድሩ አካላት የስራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን የማስተዳደር አቅም ይፈጥርላቸዋል፡፡

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

  • ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን እና ሻወር ቤቶችን በጥቅል መገንባት፤

የአፈፃፀም ስልቶች

  • የግንባታ ስራውን በዘርፉ ልምድ ላላቸው ተቋራጮች ለመስጠት በመመዘኛው መስፈርት መሰረት ተጫረቾች ይገመገማሉ፣ለአሸናፊው ስራው ይሰጣል፤

ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የግንባታ ግብዓቶች

  • ሲሚንቶና የሲሚንቶ ውጤቶች
  • ለግንባታ የሚሆኑ የአርማታ ብረቶች
  • አሸዋ፣ጠጠር እና ድንጋይ

የክትትልና የግምገማ ስርዓት

  • -ፕሮጀክቱ በሳምንታዊና በወርሃዊ በሚቀርቡ ሪፖርቶች ይገመገማል፤
  • ፕ/ጽ/ቤቱ ለፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሀንዲስ በመመደብ ሥራውን በቅርበት ይከታተላል፤
  • የፕሮጀክቱን ውጤትና የደረሰበትን ደረጃ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

ስጋትና ምቹ ሁኔታዎች

  • ፕሮጀክቱ የሚያጋጥሙት ስጋቶች
  • የግንባታ ቦታ ዕጥረት
  • ምቹ ሁኔታዎች
  • መንግስት ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን እና ሻወር ቤቶችን እንዲስፋፉ እና ያሉትም በአግባቡ አገልግሎት እንዲሰጡ የሰጠው ትኩረት፤

በጀት

  • ለፕሮጀክቱ በጠቅላላው 15,359 ብር በጥቅል ተይዞለታል፡፡
ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
48 የBio-gas የህዝብ መጸዳጃ ቤት ጥናትና ግንባታ ፕሮጀክት   15,359 0 15,359 0 0
48.1 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የባዮጋዝ ዳይጀስተር ግንባታ ማከናወን 614,358 15,359 15,359 የግንባታ ስራው ሙሉ በሙሉ የሚያልቅ በመሆኑ ለቀጣዩ የ2008 በጀት አመት ቀሪ የ2.5 በመቶ የመያዣ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡