የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የከተማውን የውሃ አቅርቦት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ ቢመጣም የአዲስ አበባ ከተማን የእድገት ደረጃ የሚመጥን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከገፀ- ምድና ከከርሰ ምድር የውሃ ምንጮች ለማሟላት ከአጭር ጊዜ እስከ ረጅም ጊዜ የሚፈፀም ዕቅድ በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ በተለይ ባለፉት አመታት በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፡፡

በ2011 በጀት ዓመት በከተማዋ የከፋ የውኃ አቅርቦት ችግር በሚታይባቸው አካባቢዎች የሚታየውን የውኃ አቅርቦት ችግር ለማቃለል በተመረጡ የከተማዋ ኪስ ቦታዎች በገርጂ፣ በአንቆርጫ፣ በኮከበ ጽባህ፣በኮሰጣ ሰፈር ፣በቦሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አከባቢ እና በራስ ስዩም አካባቢ የከረሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አቶ ጋሻው መንግስቴ የከርሰ ምድር ውሃ ምርት አቅርቢ ንዑስ የስራ ሂደት ተወካይ ገልጸዋል፡፡

በነዚህም የውሃ ፕሮጀክቶች ከ35 ሺ በላይ በአከባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን የፕሮጀክቶቹ አጠቃላይ  ግንባታ ሙሉሙሉ በራስ አቅም መከናወናቸው ሀልፊው ተናገረዋል፡፡

በተጨማሪም የውሃ እጥረት በሚታይባቸው የከተማዋ አካባቢዎች  በቤቴል ፣ በካራ ገቢሳ ፣ በጀሞ ሚካኤል፣ በእግዚአብሄር አብ፣ በቤተመንግስት፣ በመካኒሳ እና በአለም ባንክ  የከረሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ በአሁኑ ጊዜ እየተፈጠነ ሲሆን እሰከ  2012 ዓ.ም  መጨረሻ ወራት ድረስ  ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው  ወደ ስርጭት እንዲሚገቡ አቶ ጋሻው ጠቁመዋል ፡፡