የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከዚህ በታች በተጠቀሰው ክፍት የሥራ መደብ ላይ የውጭ አመልካቾችን አወዳድሮ በኮንትራት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

የሥራ መደቡ መጠሪያ ፡ሲኒየር አካውንታንት

ደረጃ ፡- 12

ብዛት፡- 5

ደመወዝ፡- 13,24ዐ

ተፈላጊ ችሎታ ፡- በአካዉንቲንግ/በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ኮሌጅ ዲፕሎማ ሆኖ 4/8 ዓመት በሲስተም ታግዞ በደብል ኢንትሪ የሂሣብ መዝጋት ልምድ ያለው/ላት በተጨማሪም የኮምፒውተር እውቀት ያለው/ላት

ማሳሰቢያ፣

1. አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7/ሰባት/ (ከህዳር 15 እስከ 23/2ዐ12 ዓ.ም) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ መገናኛ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ዋና መ/ቤት አጠገብ በሚገኘው የባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት የሰው ኃይል አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 139 በመቅረብ ካሪኩለም ቪቴ፣ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

2. መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና የግል ድርጅቶች የሚቀርቡ የሥራ ልምድ ማስረጃዎች የስራ ግብር የተከፈለበት ስለመሆኑ የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡

3. ለሥራ መደቡ የሚቀርበው የሥራ ልምድ ከምረቃ በኋላ የተገኘና ቀጥተኛ ግንኙነት (Direct Related) ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡

4. በደረጃ (Level) ለሚቀርቡ የትምህርት ማስረጃ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC) አብሮ መያያዝ ይኖርበታል፡፡

5. የቅጥር ሁኔታ፣ በኮንትራት

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
ስልክ ቁጥር፡- 011-618 76 55