የኘሮጀክቱ ሥም፡    የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ የፍሳሽ መስመር ጥናት ግንባታ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡-በአዲስ አበባ ከተማ በቃሊቲ ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙ ክፍለ ከተሞች የሚያጠቃልል ሲሆን የፍሳሽ መስመሮቹ ጥናትና ዲዛይን የሚያከናወነው በ 2002 እንደ እ.ኢ.አ  በተጠናው የፍሳሽ ማስተርፕላን የሚያካትታቸውን ቦታዎች ታሣቢ በማድረግ ይሆናል፡፡

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- በቃሊቲ ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙትን የፍሳሽ መስመር ያልተደረሰባቸውን ክፍለ ከተሞችና አካባቢዎች እንዲሁም የተገነቡትንና አዲስ የሚገነቡትን የኮንዶሚኒየም ቤቶች እና ሌሎች አካባቢዎች የፍሳሽ አገልግሎት በማዳረስ በተፋሰሱ ውስጥ የሚገኙትን ተጠቃሚ ማድረግ ይሆናል፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡-የቃሊቲ የፍሳሽ ማጣሪያ የማስፋፋት ሥራ የፍሳሽ መስመር ጥናትና ግንባታ በማከናወን የማጣሪያ ጣቢያው አሁን ያለውን የማጣራት አቅም ከ7,500 ሜ.ኩብ/በቀን ወደ 100,000 ሜ.ኩብ/በቀን በቀን በማሳደግ ተጨማሪ ወደ 1 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም እንዲፈጠር ይደረጋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ
  • የፍሳሽ ማጣሪያ ማሻሻያና ማጠናከሪያ ግንባታ ሥራ
  • የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራ

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2002 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2009 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 1,500,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እ.ኤ.አ በ2001—2002 ዓ.ም የአዲስ አበባን የፍሳሽ ማስተር ፕላን ክለሳ ኔድኮ (NEDECO) በተባለ አማካሪ አማካኝነት ማስጠናቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም ማስተር ፕላን ከተማ መሠረት የቃሊቲ ፍሳሽ ተፋሰስ ፕሮጀክት ሁለት ዋና ዋና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

እነዚህም፡

ሀ/ የቃሊቲ የፍሳሽ ተፋሰስ  መስመር ግንባታ’ ጥናትና ዲዛይን

ለ/ የቃሊቲ አካባቢ የፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታ ናቸው

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት፡-

የቃሊቲ ተፋሰስ አካባቢ በፈጣን እድገት በመልማት ላይ ያለ ሲሆን ከተወሠኑ ጥቂት አካባቢዎች በስተቀር በቂ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር የሌለው ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚገኘው የፍሳሽ ማጣሪያ አቅም አሁን ካለው የተፋሰሱ እድገት ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡

በቃሊቲ ፍሳሽ ተፋሰስ ብዛት ያላቸው ኮንደሚኒየም ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ የተገነቡትም ተገቢ የሆነ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች የላቸውም፡፡ በተጨማሪም እንዱስትሪዎች እና ሌሎች የልማት ድርጅቶች ሥራዎች በማፋጠን ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህም መሠረት ከፍተኛ የሆነ የፍሳሽ ማስወገጃ ፍላጉቶች ከሕብረተሰቡ ቀርበዋል፡፡ ስለዚህ የዚህ ፕሮጀክት ተግባራዊ መሆንም እ.ኢ.አ ከ2020—2025 ያለውን የፍሳሽ የማስወገድ ፍላጎት በተገቢ ሁኔታ ምላሽ ይሰጣል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ፡-

ቃሊቲ ፍሳሽ ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙ ፍሳሽ መስመር ያልተደረሰባቸውን አካባቢዎች የተገነቡትንና አዲስ በመገንባት ላይ ያሉትን የኮንደሚኒየም ቤቶች ፋብሪካዎች ልማት ድርጅቶች ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር በማቀናጀት ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር በማቀናጀት የፍሳሽ ማሰባሰቢያ መስመሮችንና የፍሳሽ ማጣሪያ ፕላንት እንዲገነባ በማድረግ የህብረተሰቡን ፍላጎት እና ጤንነት በመጠበቅ ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ፡-

የቃሊቲ የፍሳሽ ማጣሪያ የማስፋፋት ሥራ የፍሳሽ መስመር ጥናትና ግንባታ በማከናወን የማጣሪያ ጣቢያው አሁን ያለውን የማጣራት አቅም ከ7,500 ሜ.ኩብ/በቀን ወደ 100,000 ሜ.ኩብ/በቀን በቀን በማሳደግ ተጨማሪ ወደ 1 ሚሊየን የሚጠጋ  ህዝብ( Population Equivalent) ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም እንዲፈጠር ይደረጋል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች፡-

ሥራውን ተግባራዊ በማድረግ በአካባቢው የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች@ የኮንዶሚኒየም ቤቶች@ ድርጅቶች እና ፋብሪካዎች የዘመናዊ ፍሳሽ መስመር አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

በዚህም ፡-

  • ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
  • የአካባቢው ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡
  • የአካባቢ ብክነትን ማስወገድና የተሟላ ጤና እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
  • የፀዳች አዲስ አበባ ብሎም ለቱሪዝም እንዱስትሪ እድገት የተመቻቸ ከተማ እንድትኖረን ያደርጋል፡፡
  • ተጨማሪ የመስኖ ሥራዎችን ለመስራት የተጣራውን ፍሳሽ ለአካባቢው ግብርና እንዲውል ማድረግ ይቻላል፡፡
  • የተጣራውን የፍሳሽ ለከርሰምድር ማሟያ (Ground Water recharge) እንዲውል ማድረግ ይቻላል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • ከቀሪ 92.7 በመቶ የማጣሪያ ግንባታ ውስጥ 3 በመቶ የማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ሥራ በማከናወን ግንባታውን 96 በመቶ ማድረስ፣
  • ለ18 ኪ.ሜ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ የቧንቧና መገጣጠሚያ አቅርቦት ሥራ ቀሪ 50 በመቶ ማጠናቀቅ፣
  • ከ 18 ኪ.ሜ. የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ውስጥ የ2 ኪ.ሜ ዝርጋታ ሥራ ማከናወን፣
  • የወሰን ማስከበር ሥራ ማጠናቀቅ
  • የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን

የአካባቢ እና ነባራዊ ሁኔታዎች

በአማካሪ ድርጅት ከሚቀርቡ ጥናቶች አንዱና ዋነኛው ፕሮጀክቱ ሊያስከትለው የሚችለው አካባቢያዊ ተጽዕኖ ግምገማና ፕሮጀክቱን ተከትሎ የሚመጡ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዩች በጎና አሉታዊ ተጽእኖዎች የሚጠኑበት የጥናቱ ክፍል ነው፡፡

በጥናቱ መሠረት አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለማስቀረትና በጎ ጎኖችን ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ ያሰራል፡፡

የክትትልና ግምገማ ሥርዓት፡-

በአማካሪው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ጥናቱን በሚገመግሙ ባለሙያዎች እየታዩ መዳበር የሚገባቸው ነጥቦች እንዲዳብሩ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የክትትል መመዘኛ ነጥቦችን በጨረታና በስምምነት ሰነዶች ላይ እንዲኖር ያደርጋል፡፡

የ2008 በጀት ፍላጎት

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
12 የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ የፍሳሽ መስመር ጥናትና ግንባታ ፕሮጀክት   1,266,204,857 14,605,817 0 1,251,599,040 0
12.1 የማጣሪያ ጣቢያ ግንባታና ተያያዥ ሥራዎች ማከናወን 826,914,565 760,509,151 760,509,151 የLC እና የቅድመ ክፍያን ጨምሮ በ2008 በጀት አመት ከመያዥያ ክፍያ ውጪ ያለው  በጀት በ2008 እንዲያዝ ተደርጓል
12.2 የ18ኪ.ሜ. የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራ ማከናወን 701,154,911 456,097,166 456,097,166 የLC እና የቅድመ ክፍያን ጨምሮ በ2007 በጀት አመት የሚከፈል ሲሆን ቀሪው ክፍያ ከመያዥያ ክፍያ ውጪ ያለው  በሚቀጥለው የበጀት አመት ማለትም በ2008 እንዲያዝ ተደርጓል፡፡
12.3 የሱፐርቪዥን ሥራ ክፍያ 44,201,334 34,992,723 34,992,723 በተገባው ውለታ መሠረት ለግንባታ ቁጥጥር ለድርጅቱ በ2008 በጀት ዓመት የሚከፈል በጀት ነው፡፡
12.4 የካሳ ክፍያ መፈጸም 14,605,817 14,605,817 14,605,817 ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡