በአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባሰልጣን እየተሰጠ የሚገኘው የመሪነት ስልጠና(FLL) እራሳችንን መቀየር እንድንችል ረድቶናል አሉ የስልጠናው ተካፋይ ሰራተኞች ፡፡

ባለስልጣኑ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ እና የሰራተኛውን የባለቤትነት ስሜት ለማሳደግ የሚያስችል በዓይነቱ ለየት ያለ የመሪነት ስልጠና ከመስከረም 19/2012 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ ይገኛል ፡፡ (Field Level Leadership ) ስልጠና የአስተሳሰብ ለውጥ እንደዲያመጡ እንደረዳቸው የተናገሩት ሰልጣኞቹ፤ ከዚህ ቀደም ይህ በሀላፊ እንጂ አይፈታም ያሉት በርካታ ችግር በራሳቸው መፈታት የሚችል መሆኑን...

የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ አሁን እያጣራ ካለው 40ሺ ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ 60 ሺህ ከፍ ለማድረግ እየተሰራ ነው ፡፡

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ ሰብስቦና አጣርቶ ከሚያስዎግድባቸው ፕሮጀክቶች መካከል የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ዋናውና ትልቁ ነው፡፡ ይህ ማጣሪያ ጣቢያ በቀን 100 ሺህ ሜ.ኩብ የማጣራት አቅም ያለው ሲሆን አሁን ላይ ግን እያጣራ ያለው በቀን 40 ሺህ ሜ.ኪዩብ ብቻ ነው፡፡ በዚህ በጀት አመት ግን በቀን 60 ሺህ ሜ.ኩብ እንዲያጣራ እየሠራ መሆኑን በባለስልጣኑ የፍሳሽ ዘርፍ...

ባለስልጣኑ የውሃ አገልግሎት ክፍያ ባልፈጸሙ ደንበኞች ላይ አገልግሎቱን የማቋረጥ እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባስልጣን 56ሺ በላይ የሚሆኑት የጋራ መኖሪያ ቤት ደንበኞች የውሃ አገልግሎት ክፍያ እየፈጸሙ አይደለም፡፡ ይህም ከ80 በመቶ በላይ ወጪውን ከውሃ ሽያጭ የሚሸፍነው ባስልጣኑ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮበታል፡፡ ባለስልጣኑ የክፍያ ስርዓቱን በማዘመን እና ይበልጥ ተደራሽ በማድረግ ከሀምሌ 26/2011 ዓ.ም ጀምሮ በኢትጵያ ንግድ ባንክ በኩል ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ይህንን የተሳለጠ የክፍያ ስርአት በመጠቀም...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ቆሚ ኮሚቴ የውሃ እና ፍሳሽ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን እያሰራው የሚገኘውን የሳውዝ አያት ኖርዝ ፈንታ የውሃ ፕሮጀክት እና የኮዬ ፈጬን ያልተማከለ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ባሳለፍነው ቅዳሜ ነው የመስክ ጉብኝት ያደረገው ፡፡ የተጎበኘው የሳውዝ አያት ኖርዝ ፈንታ የውሃ ፕሮጀክት ፊዚካል ግንባታ 70 በመቶ የደረሰ ሲሆን ሲጠናቀቅ 68 ሺህ ሜ.ኪዩብ በቀን የማምረት አቅም ያለው እና ከ700ሺኅ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው...

የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍሬህይወት ገብረህይወት ዛሬ የለገዳዲ ግድብ ማጣሪያ ጣቢያ እና በግድቡ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅትም ባለስልጣኑ እያካሄዳቸው ያሉት ተግባራት መልካም መሆናቸውን ጠቅሰው በቀጣይ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ በሂደቱም ቢሯቸው ለባለስልጣኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ስራስኪያጅ ኢንጅነር ዘርይሁን አባተ ባለስልጣኑ ከገጸ ምድር የሚያገኛቸውን የውሃ ሀብቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ በአከባቢ ጥበቃ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ እስካሁን በድሬ እና...

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ደንበኞች ከህገ ወጥ ግለሰቦች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳሰበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከሰጠው ኃላፊነት አንዱ እና ዋነኛው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ንፁህ የመጠጥ ውኃን ለነዋሪ እንዲያዳርስ ነው፡፡ ባለስልጣኑ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት ንፁህ የመጠጥ ውኃ አምርቶ ከማሰራጨት ባለፈ በየቀኑ ከየአካባቢው የውኃ ናሙናዎችን በመውሰድ በላቦራቶሪ ምርመራ የጥራት ደረጃውን ይፈትሻል፡፡ ፍተሻ ከሚደረግባቸው የውኃ ናሙናዎች መካከል የብክለት...