የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ከእሁድ ነሐሴ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት በኮተቤ ሰብ ስቴሽን የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመ ይህንን ችግር ለማቃለል በለገዳዲ ጥልቅ ጉድጓድ እና በለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ ኃይል እንደሚቋረጥ አሳውቆናል፡፡
በዚህም ምክንያት በየካ አባዶ፣ በየካ አያት፣ ቦሌ ሰሚት፣ ቦሌ አራብሳ፣ በአያት ኮንዶምኒየም እና በተጠቀሱት አከባቢዎች ከነሐሴ 20 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በቀጣዮቹ አምስት ቀናት የውሃ አገልግሎት ስለሚቋረጥ የባለሥልጣኑ ደንበኞች ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን