ባለለስልጣኑ የሲቢሉ የውሃ ግድብ ፕሮጀክት ፋይናንስ እንዲያደርግ የአለም ባንክን ጠየቀ፡፡

በአለም ባንክ የውሃ ሲንየር ግሎባል ዳይሬክተር ሳሮጅ ኩማር ጃህ የተመራው ልኡክ ዛሬ የድሬ እና ለገዳዲ ግድብ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት የሲቢሉ ግድብ ፕሮጀክት የፋይናንስ ጉዳይ እና በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰራውን የግድቡ ውሃ ማስተንፈሻ በሮች ጥገና ስራ ላይ ያተኮረ ውይይትም ተደርጓል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዘሪሁን አባተ የአለም ባንክ ግሩፕ ለባለስልጣኑ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፤...

በባለስልጣኑ ለፍሳሽ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጠ፡፡

ባለስልጣኑ እውቅና እና ምስጋና መርሃ ግብር ያዘጋጀው ለፍሳሽ ተሽከርካሪ ኦፕሬተሮች እና ረዳቶች እንዲሁም ለሌሎች ባለሙያዎች ነው፡፡ በዕውቅና እና ምስጋና መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ እንደገለጹት፤ ዘርፉ የከተማችን ውበት እና ጽዳት የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ እና አሁን ባለው የከተማችን ነባራዊ ሁኔታ አብዛኛው ፍሳሽ ቆሻሻ በተሸከርካሪ የሚነሳ በመሆኑ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ የባለስልጣኑን መሰረተ ልማት ጎበኙ፡፡

ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ የለገዳዲ ግድብ ማስተንፈሻ በሮች ጥገና ፕሮጀክት ፣ የተፋሰስ ልማት እና የማሰልጠኛ ተቋም ስራዎች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በስፋራው ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡ አቶ ጃንጥራር በዚሁ ወቅት ከባህዳር የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የመስክ ላይ የአመራርነት ስልጠና (FLL) ለወሰዱ ሰራተኞችም የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል፡፡ በግድቡ አካባቢ የተሰራው የተፋሰስ ልማት ስራ በጥሩ ደረጃ እንደሚገኝ...

ባለሥልጣኑ 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 42ኛው የሥራ አስፈጻሚ ም/ቤት ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት አድርጓል፡፡

ከፊታችን የካተቲ ስምንት እስከ አስራ ሁለት ድረስ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና የሥራ አስፈጻሚ ም/ቤት ስብሰባ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡ ይህ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ባለሥልጣኑ በዘጠኙም ቅ/ጽ/ቤቶችና በዋና መ/ቤት 24 ሰዓት በተጠንቀቅ የሚሰራ ኮሚቴ አቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ ባለሥልጣኑ ለእንግዶች ማረፊያ ለተዘጋጁ 143 ሆቴሎች፣ የስብሰባ አዳራሽ እና 28 ኤምባሲዎች አስፈላጊዉን አገልግሎት ለመስጠት...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሥራ አስኪያጅ ዘርፍ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የባለሥልጣኑ መሠረተ ልማቶች ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ፣ የለገዳዲ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ እና የባለሥልጣኑን የስልጠና ማዕከል ያካተተ ሲሆን በጉብኝቱ ብዙ ግንዛቤ ማግኘታቸውን አስረድተዋል። ከተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የተውጣጡት ባለሙያዎች በጎበኙት የውሃም ሆነ የፍሳሽ ስራ አድካሚ ከፍተኛ  ድካም አንዳለው ተረድተናል ብለዋል። በሁሉም ጉብኝት ጥሩ ግንዛቤ አግኝተናል ያሉት ጉብኚዎቹ ግንዛቤያቸውን...