በ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ ያለው የሳውዝ አያት ኖርዝ ፈንታ የውሃ ፕሮጀክት ስራ እየተፋጠነ ነው

ፕሮጀክቱ ከሁለት ዓመት በፊት ተጀምሮ በውጭ ምንዛሬ ፣ የወሰን ማስከበር  እና የዲዛየን ክለሳ ችግር ተቋርጦ የነበረ ሲሆን  በአሁኑ ሰአት ያለበትን ችግር በመፍታት ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል፡፡ የውሃ ፕሮጀክቱ በቀን 68ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ የማምረት አቅም ኖሮት 618 ሺህ የከተማውን ነዋሪ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የተቀረጸ ፕሮጀክት ነው ፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በፕሮጀክቱ የታቀፉ የ21 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን...