የባለስልጣኑን አፈፃፀም ለማያሳደግ የመሪነት ስልጠና የሚወስዱ ሠራተኞች ወደ ህንድ ተሸኙ

ስልጠናው በዓለም ባንክ በሁለተኛው የከተሞች የውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት አማካኝነት የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የአፈፃፀም አቅምን ለመገንባት በታቀደ ዕቅድ መሰረት የተዘጋጀ ነው፡፡ ከባለስልጣኑ የተውጣጡ ሃያ ባለሙዎች እና ሃላፊዎች ከሐምሌ 8–17 ቀን 2011 ዓ.ም ለአስር ተከታታይ ቀናት በህንድ ሃገር የአሰልጣኞች ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን ከተመለሱ ቡኃላ በቀጣይ ሁለት ዓመታት የባለስልጣኑን አጠቃላይ ሠራተኞች...