2011 በጀት ዓመት በከተማው በተመረጡ ኪስ ቦታዎች ላይ የከርሰ ምድር ውሃ በማልማት 35 ሺ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የከተማውን የውሃ አቅርቦት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ ቢመጣም የአዲስ አበባ ከተማን የእድገት ደረጃ የሚመጥን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከገፀ- ምድና ከከርሰ ምድር የውሃ ምንጮች ለማሟላት ከአጭር ጊዜ እስከ ረጅም ጊዜ የሚፈፀም ዕቅድ በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ በተለይ ባለፉት አመታት በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፡፡ በ2011 በጀት ዓመት በከተማዋ የከፋ የውኃ አቅርቦት ችግር በሚታይባቸው...