የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በተሸው በጀት አመት ከ 2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

ባለስልጣኑ የስራ እድል የፈጠረው በ2 መቶ 29 ማህበራት ለተደራጁ 2 ሺህ 112 ወጣቶች ነው ፡፡ የስራ ዕድሉ የተፈጠረው በውሃና ፍሳሽ መስመር ቁፋሮ ፣ በጥበቃ ስራ ፣ በገንዘብ ስብሰባ፣ በውሃ ቆጣሪ ንባብ ፣ የመጸዳጃ ቤትና የሻወር ቤት አገልግሎት እና የግንባታ ስራዎች  ነው ፡፡ ለወጣቶቹ የተፈጠረው ስራም በገንዘብ ሲተመን ከ350 ሚሊየን ብር በላይ ነው ፡፡ በአጠቃላጠይ በባለስልጠኑ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ብቻ...