ባለስልጣኑ በ2012 በጀት ዓመት 1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ፡፡

ገቢውም ከውሃ ፍጆታ ክፍያ እና የተለያዩ የገቢ ርእሶች የተሰበሰበ ነው፡፡ በበጀት ዓመቱ ከተያዘው ዕቅድ አኳያም 86 % ማሳካት ተችሏል፡፡ የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከአራት መቶ ሰባ ሚሊዮን ብር (470,000, 000) ብር በላይ ብልጫ አለው፡፡ ለገቢ አሰባሰብ ማደግ ዋነኛ ምክንያቶችም የክፍያ ስርዓት ተደራሽነት እና ዘመናዊነት በማሳደግ ከለሁሉ ክፍያ ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በአቃቂ ቃሊቲ የከርሰ ምድር ውሃ አቅርቦት (GW3) ስር የሚገኙ አምስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች በኤሌትሪክ መቆራረጥ ምክኒያት በተፈጠረ የፓምፕ ብልሽት ሙሉ በሙሉ ስራ አቁመዋል።

ጉድጓዶቹ ስራ ያቆሙት ባለፉት ተከታታይ አምስት ቀናት ባጋጠመው የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ ምክንያት ሲሆን ፓምፖቹን ጠግና ወደስራ ለመመለስ እየተሰራ ይገኛል። ሆኖም ጥገናው ከ10 ቀናት በላይ ሊወስድ ስለሚችል በተለይ በሳሪስ፣ አዲስ ሰፈር፣ ቄራ፣ ሳር ቤት፣ ደምበል ጀርባ፣ ስታዲየም፣ ኤርፖርት እና ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢዎች የውሃ አቅርቦት ችግር ይፈጠራል። ጉድጓዶቹ በቀን 17,539 ሜ.ኩብ ውሃ የሚሰጡ ሲሆን በእነዚህ...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በ2013 በጀት አመት አርባ ዘጠኝ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለማልማት አቅዷል፡፡

ባለስልጣኑ የመዲናዋን የመጠጥ ዉሃ እጥረት ለመቅረፍ በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ ወደ ስርጭት የሚገቡ የውሃ ልማት አማራጮች ላይ እቅድ በመያዝ ተግባራዊ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት በተያዘው በጀት አመት በአጭር ጊዜ ወደ ስርጭት ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁ 49 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን በማልማት መቶ ሺህ (100,000) ሜትር ኪዩብ ውሃ ለማረት እቅድ ይዞ ነዉ እየሰራ የሚገኘው ፡፡ ባለስልጣኑ በበጀት አመቱ...