ባለሥልጣኑ 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 42ኛው የሥራ አስፈጻሚ ም/ቤት ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት አድርጓል፡፡

ከፊታችን የካተቲ ስምንት እስከ አስራ ሁለት ድረስ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና የሥራ አስፈጻሚ ም/ቤት ስብሰባ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡ ይህ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ባለሥልጣኑ በዘጠኙም ቅ/ጽ/ቤቶችና በዋና መ/ቤት 24 ሰዓት በተጠንቀቅ የሚሰራ ኮሚቴ አቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ ባለሥልጣኑ ለእንግዶች ማረፊያ ለተዘጋጁ 143 ሆቴሎች፣ የስብሰባ አዳራሽ እና 28 ኤምባሲዎች አስፈላጊዉን አገልግሎት ለመስጠት...