ባለስልጣኑ የውሃ ቢል ክፍያን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ለማድረግ ስምምነት አደረገ

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ደንበኞች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ክፍያ መፈጸም የሚያስችላቸውን ስምምነት  አደረገ፡፡ በስምምነቱ መሰረት ባንኩ በከተማዋ ለሚገኙ የውሃ ደንበኞች በአራት አይነት የአከፋፈል ስርዓት ማለትም በሞባይል ባንኪንግ፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ከተቀማጭ በሚቀነስ ሂሳብ እና በባንኩ ቅርንጫፎች አማካኝነት አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ደንበኞች በባንኩ መስኮት ለሚያገኙት አገልግሎት ብቻ 2 ብር...