ፍሳሽ ቆሻሻን የማስወገድ አገልግሎት የግንዛቤ ማስጨበጫ የተዘጋጀ

በመዲናችን አዲስ አበባ ፍሳሽ ቆሻሻን የማስወገድ አገልግሎት የጀመረው በ1920ዎቹ መጨረሻ ገደማ ነው፡፡ ጅማሮው በ1920ዎቹ ይሁን እንጂ፣ ፍሳሽን በዘመናዊ መልኩ በመስመር የማስወገድ ሥራው ከቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ መጠናቀቅ ጋር ተያይዞ በ1974 ዓ.ም ተግባራዊ እንደተደረገ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመቀጠልም በ1993 በቀን 3,000 ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ የመቀበል አቅም ያለው የኮተቤ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታው...