የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ ስርጭቱን ለማሻሻል እየሰራ ነው፡፡

ባለስልጣኑ ባለፍት ስድስት ወራም 5 ኪሎ.ሜ ከፍተኛ እና ከ60 ኪ.ሜ በላይ መለስተኛ የውሃ መስመር ዘርግቷል፡፡ የውሃ መስመር ዝርጋታው የሚያከናውነው በከፍተኛ በመካከለኛ እና አነስተኛ መስመር በመከፋፈል ሲሆን ከፍተኛው በዋናው መ/ቤት እና ፕሮጀክት ጽ/ቤት ፤ መካከለኛ እና አነስተኛ መሽመሮች ደግሞ በቅርንጫፍ ጽ/ቤት አማኝነት የተዘረጉ ናቸው፡፡ የውሃ መስመሮቹም የተዘረጉት የመንገድ ስራ በሚሰራቸው አካባቢዎች፣የጋራ...

ውሃ ከምርት እስከ ተጠቃሚው ለመድረስ የሚያልፍባቸውን ሂደቶች ያውቃሉ?

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከገፀ-ምድር እና ከርሰ-ምድር የሚያመርተውን የተጣራ ንፁህ ውሃ ለተጠቃሚው ለማድረስ ከ8 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የውሃ መስመሮችን ዘርግቷል፡፡ ንፁህ የመጠጥ ውሃ በእነዚህ መስመሮች አማካኝነት ደንበኞች ጋር የሚደርሰው በርካታ ማጠራቀሚያዎችን እና ግፊት መስጫዎችን አልፎ ነው፡፡ በከተማዋ ውስጥ በአጠቃላይ 90 የውሃ ማጠራቀሚ እና ግፊት መስጫ ጣቢያዎች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ 55ቱ የውሃ...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በአንድ ቅ/ጽ ቤት ተግባራዊ ማድረግ የጀመረውን የዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት ወደ አራት ከፍ አደረገ ፡፡

በዚህ ወር ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት ተግባራዊ የተደረገባቸው አራዳ፣ ጉለሌ እና መገናኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሲሆኑ ፡- በጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ስር ፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 8 ፣ አራዳ ክ/ከተማ ከወረዳ 2 እስከ 7፣ የካ ክ/ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 4 የሚገኙ ከ55,000 በላይ ደንበኞች ፤ አዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ስር ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9እና 10፣ አዲስ ከተማ ክ/ከ ወረዳ 4፣5፣6፣7፣9፣እና 10፣...

በአለም ባንክ ግሩፕ የውሃ ግሎባል ዳይሬክተር ጄኒፈር ጄ ሳራ የባስልጣኑን የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ጎበኙ፡፡

ዳይሬክተሯ ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የሂሳብ መዝጋት እና ኦዲት ስራ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡ ባለስልጣኑ አሁን እየሰራ ያለውን ስራ እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራአስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ አጭር ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ባለስልጣኑ እየሰጠ ስላለው የአቅም ግንባታ ስልጠና እና እያመጣ ያለውን ለውጥ በተመለከተም ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ ዳሬክተሯ ጄኒፈር ጄ ሳራ...

የአዲስ አባባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ምስራቅ አዲስ አበባን የዘመናዊ ፍሳሽ ማሰወገድ ስርዓት ተጠቃሚ ለማድረግ የጥናት እና ዲዛይን ስራ አስጀመረ፡፡

የጥናት እና ዲዛይን ስራው በዋናነት በከተማዋ ምስራቃዊ ክፍል በተለይም በቦሌ እና በየካ ክፈለ ከተሞች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ ፕሮጀክቱም በቀን ሰማንያ ሺ (80,000) ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ ቆሻሻ በዘመናዊ መንገድ አጣርቶ የሚያሰወግድ ሲሆን አሁን በከተማዋ ያለውን ፍሳሽ በመስመር የማስወገድ ዝቅተኛ ሽፋን የሚሳድገው ይሆናል፡፡ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ዲዛይንና ጥናት ከዓለም ባንክ በተገኝ 6.7...