አንጋፋው የባለስልጣኑ ሠራተኛ አረፉ።

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን ለ42 ዓመታት በተለያዩ ሃላፊነቶች ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ እምሩ መኮንን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በ70 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ አቶ እምሩ ከአባታቸው አቶ መኮንን ንጉሴ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አድጋልኝ ቦጋለ በቀድሞው ወለጋ ጠቅላይ ግዛት በአሁኑ ምስራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ ኮኒሳ ቀሌ 01 ቀበሌ በሰኔ ወር 1942 ዓ.ም ነው የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ...

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን በኪራይ ቤቶች የሚኖሩ ደንበኞችን ቅሬታ የሚፈታ ስራ ጀመረ::

በባለስልጣኑ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከኪራይ ቤቶች አስተዳደር ጋር የሚገባውን ውል በማስቀረትና ወሉን በቀጥታ ከተከራዮች ጋር በማድረግ በኪራይ ቤቶች አስተዳደር ህንፃዎች የሚኖሩ ደንበኞች ከውሃ አገልግሎት እና ክፍያ ጋር ሲያጋጥማቸው የነበረውን ውጣ ውረድ ለማስቀረት የሚያስችለል የማስተካከያ እያደረገ ነው ፡፡ የማስተካከያ ስራው በቅርንጫፉ ስር በሚገኙ 42 የኪራይ ቤት ህንፃዎች በዘፈቀደ በማድ ቤት እና ለንባብ አመቺ...

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን ወላጆቻውን በተለያየ ምክኒያት ላጡ እና ባለስልጣኑ ለሚያሳድጋቸው 22 ህጻናት እና ታዳጊዎች የገና በዓል መዋያ ስጦታ አበረከተ፡፡

ባለሥልጣኑ የማህበራዊ አገልግሎቱን ለመወጣት ላለፉት ስምንት ዓመታት ለታዳጊዎች እና ህጻናት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ድጋፉን የሚደረገውም ከሰራተኞች በሚሰበሰብ የገንዘብ መዋጮ ሲሆን በየውሩ ለእያንዳንዳቸው 600 ብር ይደርሳቸዋል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በዋና ዋና በአላት ወቅት ለበአሉ መዋያ የሚሆናቸው ስድስት መቶ ብር በነብስ ወከፍ በተጨማሪነት በስጦታ መልክ ለቤተሰቦቻቸው ወይም ለአሳጊዎቻቸው...

ነዋሪዎች የመፀዳጃ ቤት አጠቃቀማቸውን ማስተካከል እንዳለባቸው የደንበኞች ፎረም ተወካዮች አሳሰቡ።

የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን የጎበኙት የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደንበኞች ፎረም ተወካዮች በፍሳሽ ቆሻሻ ማንሳት፣ ማጣራት እና ማስወገድ ላይ በቂ ግንዛቤ ማግኘታችውንና በአከባቢያቸው በግንዛቤ እጥረት ምክንያት በመፀዳጃ ቤት አጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ገልፀዋል። ከጎብኝዎች መካከል እስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ይድነቃቸው አስራቱ ከየቤቱ የሚነሳው ፍሳሽ ቆሻሻ ሜዳ ላይ የሚደፋ ሳይሆን ከፍተኛ...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት ተግባራዊ አደረገ ፡፡

ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓቱ ተግባራዊ የተደረገው በባለስልጣኑ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስር ባሉ 18 ወረዳዎች ሲሆን በጥቅሉ 47000 (አርባ ሰባት ሺህ ) ደንበኞች ላይ ነው፡፡ ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርአቱ የቆጣሪ ጥራት ችግርን እና ግምታዊ አሞላልን ከማስቀረት ባለፈ ደንበኛው የውሃ ፍጆታውን በተጠቀመበት ወር ለመክፈል ያስችለዋል ፤ ከዚህም ባለፈ የገቢ አሰባሰብ ስርአቱን ከማሳለጥ አንጻር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ፡፡...