የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የፉሪ ሀና የጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮጀክት ዋና የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ በራስ ሀይል እያከናወነ ነው ።

የባለስልጣኑ የፍሳሽ ዘርፍ ም/ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢ/ር አለማየሁ መንግስቱ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታን ለማፋጠን በ4 ቡድን የተደራጀ የራስ ሀይል በማስገባት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል...
የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ሰራተኞች እና አመራሮች  ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መረሀ ግብሩን አጠናረው ቀጥሏል ፡፡

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ሰራተኞች እና አመራሮች ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መረሀ ግብሩን አጠናረው ቀጥሏል ፡፡

ዛሬም በባለስልጣኑ ዋናው መስሪያ ቤት “ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ” በሚል መሪ ቃል ደም ለግሰዋል፡፡ በመረሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ወርቁ አንዱዓለም የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ዓላማ የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ሀገር አፍራሾችን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ለሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ሰራተኛው የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው ብለዋል።...