ንብረትነቱ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የሆነው የፍሳሽ መሰረተ ልማት ላይ ባእድ ነገር ሲጨምሩ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የፋብሪካ ተረፈ ምርት በቦቴ ተሸከርካሪ በማጓጓዝ እና በባለስልጣኑ የፍሳሽ መስመር ውስጥ በመድፋታቸው ነው፡፡ በተደጋጋሚ በፍሳሽ መሰረተ ልማቱ ላይ የፋብሪካ ፍሳሽ ተረፈ ምርት በመደፋቱ የመዲናዋን ፍሳሽ አወጋገድ ዘመናዊ ለማድረግ በከፍተኛ ወጪ የተገነባው የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እና ባዮሎጂካል ክፍሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ ይህንንም ችግር ለመቅረፍ...

በአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ከፍተኛ የውሃ መስመር ላይ ጉዳት ያደረሱ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች 2 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ እንዲከፍሉ ተወሰነባቸው፡፡

ውሳኔውን ያስተላለፉት የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ እና የአቃቂ ምድብ ችሎት ናቸው፡፡ ሲሲሲሲ በመባል የሚታወቀው የቻይና ኮሙኒኬሽን እና ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ቃሊቲ በሚገኛው የባለስልጣኑ ከባድ መስመር ላይ ጉዳት ማድረሱን የተመለከተው የልደታ ምድብ ችሎት ድርጅቱ ላደረሰው ጉዳት እና ኪሳራ አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ሁለት ሺ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ብር (1,752,247) ካሳ እንዲከፍል ውሳኔ...

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ ስርጭቱን ለማሻሻል እየሰራ ነው፡፡

ባለስልጣኑ ባለፍት ስድስት ወራም 5 ኪሎ.ሜ ከፍተኛ እና ከ60 ኪ.ሜ በላይ መለስተኛ የውሃ መስመር ዘርግቷል፡፡ የውሃ መስመር ዝርጋታው የሚያከናውነው በከፍተኛ በመካከለኛ እና አነስተኛ መስመር በመከፋፈል ሲሆን ከፍተኛው በዋናው መ/ቤት እና ፕሮጀክት ጽ/ቤት ፤ መካከለኛ እና አነስተኛ መሽመሮች ደግሞ በቅርንጫፍ ጽ/ቤት አማኝነት የተዘረጉ ናቸው፡፡ የውሃ መስመሮቹም የተዘረጉት የመንገድ ስራ በሚሰራቸው አካባቢዎች፣የጋራ...

ውሃ ከምርት እስከ ተጠቃሚው ለመድረስ የሚያልፍባቸውን ሂደቶች ያውቃሉ?

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከገፀ-ምድር እና ከርሰ-ምድር የሚያመርተውን የተጣራ ንፁህ ውሃ ለተጠቃሚው ለማድረስ ከ8 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የውሃ መስመሮችን ዘርግቷል፡፡ ንፁህ የመጠጥ ውሃ በእነዚህ መስመሮች አማካኝነት ደንበኞች ጋር የሚደርሰው በርካታ ማጠራቀሚያዎችን እና ግፊት መስጫዎችን አልፎ ነው፡፡ በከተማዋ ውስጥ በአጠቃላይ 90 የውሃ ማጠራቀሚ እና ግፊት መስጫ ጣቢያዎች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ 55ቱ የውሃ...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በአንድ ቅ/ጽ ቤት ተግባራዊ ማድረግ የጀመረውን የዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት ወደ አራት ከፍ አደረገ ፡፡

በዚህ ወር ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት ተግባራዊ የተደረገባቸው አራዳ፣ ጉለሌ እና መገናኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሲሆኑ ፡- በጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ስር ፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 8 ፣ አራዳ ክ/ከተማ ከወረዳ 2 እስከ 7፣ የካ ክ/ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 4 የሚገኙ ከ55,000 በላይ ደንበኞች ፤ አዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ስር ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9እና 10፣ አዲስ ከተማ ክ/ከ ወረዳ 4፣5፣6፣7፣9፣እና 10፣...